ባለፉት ስድስት ወራት 20ሺ የሚሆኑ ዜጎች የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል

You are currently viewing ባለፉት ስድስት ወራት 20ሺ የሚሆኑ ዜጎች የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል

AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ገምግሟል።

በግምገማ መርሃ ገብሩ የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ የማነ ደሳለኝ ቢሮው ባለፊት ስድስት ወራት በሀገራዊና ከተማ አቀፍ ስራዎች ላይ ሲሳተፍ መቆየቱን ገልፀዋል።

20ሺ የሚሆኑ ዜጎች በኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና ሰልጥነው ስለማጠናቀቃቸው ተገልፀዋል።

በአሁኑ ሰዓትም 110ሺ ዜጎች ስልጠናውን እየተከታተሉ መሆኑንም ሀላፊው አመልክተዋል።

ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት የ4 ተቋማትን አገልግሎት ዲጂታላይዝ ማድረግ ስለመቻሉ አስታውቋል።

ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት 1 ሺህ ለሚሆኑ ባለሙያዎች የሳይበር ደህንነት ስልጠና ለመስጠት አቅዶ 3 ሺህ 700 ለሚሆኑት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ስለመቻሉም ተመላክቷል።

በፅዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review