ባለፉት ቀናት አዲስ አበባ ከተማ ያስተናገደቻቸው አህጉራዊና ዓለምአቀፍ ጉባዔዎች የከተማዋን የሁነት ተመራጭነት የሚያልቁ መሆናቸው ተገለፀ

You are currently viewing ባለፉት ቀናት አዲስ አበባ ከተማ ያስተናገደቻቸው አህጉራዊና ዓለምአቀፍ ጉባዔዎች የከተማዋን የሁነት ተመራጭነት የሚያልቁ መሆናቸው ተገለፀ

AMN-ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

ባለፉት ቀናት አዲስ አበባ ከተማ ያስተናገደቻቸው አህጉራዊና ዓለምአቀፍ ጉባዔዎች የከተማዋን የሁነት ተመራጭነትና የዲፕሎማሲ ማዕከልነት የሚያልቁ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሰሞነኛ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባተኮረ መግለጫቸው በውጭ ግንኙነት ዘርፍ የተከናወኑ እንቅስቃሴዎችን ዳሰዋል።

ባለፈው ሳምንትና ከዛም በቀደሙ ቀናት አዲስ አበባ ከተማ በርካታ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ሁነቶችን ስለማስተናገዷ አውስተዋል።

የሳይበር ደህንነት ኮንፈረንስ፣ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ኢቲኤክስ)፣ የዓለም ስራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባዔ፣ አይ ዲ ፎር (ID4) የዲጂታል መታወቂያ ጉባዔ፣ የአፍሪካ መድን ጉባዔ እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ሁለት ቀጠናዊ ምክክሮችን ለማሳያ ጠቅሰዋል ቃል አቀባዩ።

በርካታ ተሳታፊዎችና እንግዶችን ያሳተፉት እነዚህ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ሁነቶች በስኬት የተጠናቀቁ ከመሆናቸው በላይ የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ማሳደግ የሚያስችል መደላድል የተፈጠረባቸው እንደሆኑም ገልፀዋል።

አዲስ አበባ ከተማም መሰል ግዙፍ መድረኮችን በምቾት የማስተናገድ አቅሟን ያሳየችባቸው ብለዋቸዋል አምባሳደር ነብያት።

ከተማዋ የሁነት ተመራጭነቷን ከማሳደግ አልፎ የዲፕሎማሲ ማዕከልነትን ያፀኑ ገፅታዋንም ያላቁ ስለመሆናቸው ቃል አቀባዩ አምባሳደር ነብያት በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

በአቡ ቻሌ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review