AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም
ባለፉት አመታት በተከናወኑ ተግባራት የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች ከተማ መፍጠር እና የህዝብን ጥቅም ያረጋገጡ ሰው ተኮር ስራዎች መሰራታችውን የየካ ክፍለ ከተማ አስታወቀ ::
“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ 2ተኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል::
በኮንፍረንሱ በየደረጃው ያሉ የክፍለ ከተማው አመራሮችና የፓርቲው አባላት ተገኝተዋል ።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ፣ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ፓርቲው ሁለተናዊ ለውጥ ለማምጣት እየተጋ እንደሚገኝ ተናግረዋል ::
ፓርቲው ሀገር በቀል እውቀቶችን እና እሴቶችን ለማጎልበት ለጋራ እውነት እና አብሮነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል ስራ አስፈፃሚው::
የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና፣ ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል ::
በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ እና የሀገርን ዕድገት የሚያፋጥኑ የልማት ሥራዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ባለፉት አመታት በተከናወኑ ተግባራት የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች ከተማ መፍጠር መቻሉን የተናገሩት አቶ መገርሳ ይህ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል::
በቴዎድሮስ ይሳ