ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ከ10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል-የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

You are currently viewing ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ከ10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል-የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

AMN-ሚያዚያ 21/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባና አካባቢዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከደረሱ የእሳት እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ከ10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከዉድመት ማዳን መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽኑ አስታዉቋል።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ 454 አደጋዎች ያጋጠሙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 303 የሚሆኑት የእሳት አደጋዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 151ዱ ድንገተኛ አደጋዎች እንደሆኑ ተገልጿል።

በደረሱት አደጋዎች ከ 556 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሲወድም የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ከ10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን መቻሉ ተመላክቷል።

በደረሱት አደጋዎች ምክንያት ህይወታቸዉ አደጋ ውስጥ የነበረ 104 ሰዎችን መታደግ መቻሉም ተብራርቷል።

ካጋጠሙት አደጋዎች ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው በመኖሪያ ቤቶች ላይ ያጋጠመ አደጋ ሲሆን በንግድ ቤቶች ላይ ያጋጠሙ አደጋዎች በሁለተኝነት ተቀምጠዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ እና አካባቢዋ የደረሱ አደጋዎችን በፍጥነት መቆጣጠር በመቻሉ ከፍተኛ ሀብት ከውድመት ማዳን መቻሉን የተገለጸ ሲሆን ይህም ኮሚሽኑ አደጋዎችን ፈጥኖ በመቆጣጠር የማዳን አቅሙ 97 በመቶ መድረሱን እንደሚያሳይ መገለጹን የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል።

በከተማዋ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግና የጥንቃቄ ባህልን በማሳደግ አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል የሚቻል በመሆኑ ህብረተሰቡ ከኮሚሽን መ/ቤቱ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን መተግበሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review