ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ40 ሺህ በላይ አዳዲስ የሠላም ሠራዊት አባላት ወደ ዘርፉ ተቀላቅለዋል- ቢሮው

You are currently viewing ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ40 ሺህ በላይ አዳዲስ የሠላም ሠራዊት አባላት ወደ ዘርፉ ተቀላቅለዋል- ቢሮው

AMN-መጋቢት 23/2017 ዓ.ም

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ40 ሺህ በላይ አዳዲስ የሠላም ሠራዊት አባላት በማሰልጠን ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ መደረጉን የአዲስ አበባ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።

የአዲስ አበባ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ3ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና በጫኝና አውራጅ ማህበራት የኢንስፔክሽን ግኝት ላይ በማተኮር ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄዷል።

የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ ቢሮው በበጀት ዓመቱ በ8 ግቦች ላይ አተኩሮ በማቀድ ወደ ትግበራ የገባ መሆኑን እና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ስኬታማ ስራ መሠራቱን ተናግረዋል።

በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ35 በላይ ስኬታማ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች በመላው የከተማዋ ነዋሪ ትብብር እና በጸጥታ መዋቅሩ ቅንጅት ማካሄድ መቻሉንም አንስተዋል።

የተለያዩ የአደባባይ በዓላት የአዲስ አበባን ህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚያሳይ መልኩ መካሄዳቸውንም ነው የጠቀሱት።

ለዚህ ሁሉ ስኬት የመላው የከተማ ነዋሪ ትብብር እና ቢሮው ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን አንስተዋል።

የቢሮው ያለፉት ዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮው የጸጥታ እና ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review