የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 163 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ፣ አሁን ላይ 160.9 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ።
የቢሮው የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ እንደገለጹት፣ ቢሮው ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን ወደ ተግባር አስገብቷል፡፡
የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ሲገባቸው ሳይመዘገቡ የቀሩ ወደ 13 ሺህ ነጋዴዎችን ወደ እሴት ታክስ ስርዓት ማስገባቱንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በ2016 ዓ.ም የደመወዝ ግብር ከፋች ቁጥር 20 ሺህ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ በዘንድሮው ዘጠኝ ወራት ውስጥ ወደ 49 ሺህ ከፍ ማለቱም ተመላክቷል፡፡
በበላይሁን ፍሰሃ