ባለፉት 6 ወራት የጥራት ደረጃ ያላሟሉ 46 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል-የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

You are currently viewing ባለፉት 6 ወራት የጥራት ደረጃ ያላሟሉ 46 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል-የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

AMN – ጥር 9/2017 ዓ.ም

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ 245 ደርጅቶች ላይ የምርት ጥራት ኢንስፔክሽን መከናወኑን እና 46 ድርጅቶች የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ ያላሟሉ መሆናቸውን በገበያና ፋብሪካ ምርት ጥራት ቁጥጥር ማረጋገጥ መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት አስገዳጅ ደረጃ በወጣላቸውና በገበያና ፋብሪካዎች ላይ በሚገኙ የስጋት ደረጃቸው ከፍተኛ በሆኑ 21 የምርት አይነቶች (በ35 ድርጅቶች የተወከሉ) እንዲሁም አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርት የወጣላቸውን ምርቶችን በሚያመርቱ 210 ፋበሪካዎች በድምሩ 245 ድርጅቶች ላይ የምርት ጥራት ቁጥጥርና ክትተል (ኢንስፔክሽን) ስራ መከናወኑ ተገልጿል፡፡

የምርት ጥራት ኢንስፔክሽን ከተከናወነባቸው 245 ድርጅቶች ላይ 194 ወካይ ናሙናዎችን በመውሰድ በተደረገው የእይታ፣ ኢንስፔክሽን እና የላብራቶሪ ፍተሻ ውጤት መሰረት 77 ድርጅቶች ለምርቱ የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ ያሟሉ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል 46 ድርጅቶች የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ ያላሟሉ መሆናቸውን በገበያና ፋብሪካ ምርት ጥራት ቁጥጥር ማረጋገጥ መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል፡፡

ቀሪዎቹ 122 ድርጅቶች አስፈላጊውን መረጃዎች (የሶስተኛ ወገን የላብራቶሪ ፍተሻ ዉጤት፣ የጥራት ስርተፍኬት፣ ወቅተዊ የሥነ-ልክ የምስክር ወረቀት እንዲሁም በማምረት ሂደታቸው በተደረገው በግንባር ዕይታ/physical inspection/ መሰረት በተቀመጠው ደረጃና መስፈርት መሰረት እየሰሩ መሆኑ ለማረጋገጥ ተችሏል ነው የተባለው።

ጥራት ደረጃ ያላሟሉ 46 ድርጅቶች ወይም በ56 ወካይ ናሙናዎች የተወከሉ (6 ውኃ፤3 ቆርቆሮ፣6 የዕቃ ማሸጊያ ሳሙና ፤9 የልብስ ሳሙና፤10 አርማታ ብረት፣ 2 ዲተርጀት ዱቄት ሳሙና፤ 4 ፈሳሽ ሳሙና፣ 4 ዋየር እንዲሁም 1 ማከፋፈያ ዲቫይደር፣ 1 ፈሳሽ እጅ ሳሙና፤ 3 ኤል ኢ ዲ አምፖል፤ 2 የምግብ ጨው፤1 ፈሳሽ የማሽን ማጠቢያ ሳሙና፤1 ዱቄት ሳሙና፣1 አጃክስ ሳሙና፤1 ለውዝ ቅቤ፣ 1 የምግብ ዘይት ምርቶች የሚገኙ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የጥራት ደረጃ ያላሟሉ እነዚህ 46 ድርጅቶች ላይ ከማምረት ሂደታቸው እንዲታገዱ ከመደረጉ በተጨማሪ ምርታቸውንም ወደ ገበያ እንዳያቀርቡ እና ከገበያ ላይ እንዲሰበስቡ የተደረገ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ችግሩን ለይተው የማስተካከያ ስራ እንዲሰሩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዳቸው ተመላክቷል፡፡

ከነዚህ 46 ድርጀቶች ዉስጥ 2 የአርማታ ብረት ፋብሪካዎች ጉዳያቸው በህግ ተይዞ የወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ ለሚመለከተው የፍትህ አካላት የማስተላለፍ ሥራ መከናወኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከደረጃ በታች በመሆናቸው ለገበያ እንዳይቀርቡ እና ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ ከተደረጉ ምርቶች መካከል፡-

• 4500 ካርቶን የልብስ ሳሙና እና 543 ፍሬ ፈሳሽ የዕቃ ማጠቢያ ሳሙናዎች እንዲሁም 3,083 ፍሬ ባለ 14 እና 10 ዲያሜትር አርማታ ብረት ወደ ገበያ እንዳይወጣ በማድረግ እንዲወገድ (re-process) ተደርጓል፡፡

• 760 ጥቅል የተለያዩ መጠን ያላቸው ሁለት ፋብሪካዎች ዋይር ምርት ከገበያ ላይ እንዲሰበስብ በማድረግ እንዲወገድ ተደርጓል፡፡

• 77,356 ባለ 0.20 ሚሜ የአጥር ሽንሽን ቆርቆሮ በደረጃው መስረት not for roofing’ መግለጫ ሳይጻፍ ለገበያ ሊቀረብ የተዘጋጀ ምርት የአስተዳደራዊ እርምጃ በመወስድ በደረጃው መሰረት ተገቢው ማስተካከያ እንዲደረግ ተደርጓል፡፡

• በ3 የምርት አይነቶች 20 የተለያዩ የምርት ወካይ ናሙናዎች (14 LED Lamp፣2 Wire, & 6 የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ) በተደረገው የላበራቶሪ ፍተሻ ውጤት ያላሟላ በመሆኑ እና በተደረገው የምርት ዱካ ማጣራት አግባብ ምንጫቸው ያልታወቁ ምርቶች በመሆናቸው ሸማቹ ህብረተሰብ እንዳይጠቀም እንዲወጣ ተደርጓል፡

• 670 ጥቅል (እያንዳንዱ 1,200 ኬሎ ግራም) እና 1200 ፍሬ አርማታ ብረት እንዲሁም 4000 በላይ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ወደ ገበያ እንዳይወጣ በማድረግ የእሸጋ እርምጃ መወሰዱ ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review