ባለፉት 6 ወራት ያለደረሰኝ ሽያጭ ላይ በተካሄደ ቁጥጥር በቅጣት ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ

You are currently viewing ባለፉት 6 ወራት ያለደረሰኝ ሽያጭ ላይ በተካሄደ ቁጥጥር በቅጣት ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ

AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም

ባለፉት 6 ወራት ያለደረሰኝ ሽያጭ ላይ በተካሄደ ቁጥጥር በቅጣት ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 ግማሽ በጀት ዓመት ያለደረሰኝ ሽያጭ ላይ ባካሄደው ቁጥጥር 297 ሚሊዮን 250 ሺህ ብር ከቅጣት መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡

በቢሮው የኢንተለጀንስ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ እንደገለፁት፣ ያለደረሰኝ ሽያጭ ለመቆጣጠር በግማሽ በጀት ዓመቱ በትኩረት ተሰርቷል፡፡

በ671 የንግድ ድርጅቶች ላይ በተካሄደ የኢንተለጀንስ ስራ 632 የንግድ ድርጅቶች ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውኑ በመገኘታቸው አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች ተወሰደዋል ብለዋል፡፡

በዚህም 63 ሚሊዮን 200 ሺህ ብር ለመሰብሰብ ተችሏል ያሉት አቶ ተስፋዬ 839 ተጠርጣሪዎች ላይም ከአስተዳደራዊ ቅጣት ባሻገር የወንጀል ክስ በመመስረት ጉዳያቸው በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑን መናገራቸውን የቢሮው መረጃ ያመለክታል፡፡

የቢሮው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ልደቱ በበኩላቸው፣ በግማሽ በጀት ዓመቱ ካለደረሰኝ ሽያጭ ጋር በተያያዘ በተከናወነ ክትትልና ቁጥጥር 3 ሺህ 225 የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች ላይ ያለደረሰኝ ሽያጭ በማከናወን በተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ 234 ሚሊዮን 50 ሺህ ብር በቅጣት ገቢ ተሰብስቧል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review