ባለፉት 9 ወራት በህገ ወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ከ110 ሺ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

You are currently viewing ባለፉት 9 ወራት በህገ ወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ከ110 ሺ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

AMN-ሚያዚያ 21/2017 ዓ.ም

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ቢሾፍቱ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ይህንን አስመልክተው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርማችን መሳካት የበኩላችንን ድርሻ በብቃት ለመወጣት ያስቻሉን ውጤቶችን አስመዝግበናል ብለዋል፡፡

ከሃገር ንግድ አፈጻጸም አንጻር በኦንላይን አገልግሎት 2.6 ሚሊዮን በላይ የንግዱ ማህበረሰብ አዲስ ንግድ ፍቃድ ማውጣት፣ የንግድ ምዝገባ ማከናወንና ነባር የንግድ ፍቃድ ማደስ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

ዘንድሮ በክልሎች በተጀመረው የድሀረ ፍቃድ አንስፔክሽን ረገድም ከ2.2 ሚሊዮን በላይ የንግድ ፍቃድ እንስፔክሽን ከእቅድ በላይ አከናውነናል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡

በህገ ወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ከ110 ሺ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል፡፡

ጠንካራ የነዳጅ ግብይት ሬጉላቶሪ ሥርዓት መዘርጋትና በመተግበር አላግባብ ለመክበር በተንቀሳቀሱ የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ላይ ከ100 ሚሊዮን በላይ ቅጣት መጣሉም ተገልጿል፡፡

የሲሚንቶ ግብይት አሰራር በማሻሻል የሲሚንቶ ዋጋ ከግማሽ በታች ከመቀነስ ባለፈ ለብዙሃን በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓልም ነው ያሉት፡፡

ከወጪ ንግድ አንጻር ባለፉት 9 ወራት ብቻ በወጪ ንግድ ዘርፍ ከ5.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ መመዝገቡን አመላክተዋል፡፡

ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ ውጤት ሲሆን በበጀት ዓመቱ 150 ዕቅድ አፈጻጸም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

5ኛው የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የስራ ላይ ቡድን ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን የገለፁ ሲሆን የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት ማእቀፍ የሙከራ ንግድ ትግበራም በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ እስከ ነገ እንደሚቀጥል ተመላክቷል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review