ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገር ደረጃ የሚታዩና የሚጨበጡ ስራዎችን ሰርቷል፡- የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

You are currently viewing ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገር ደረጃ የሚታዩና የሚጨበጡ ስራዎችን ሰርቷል፡- የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

AMN – ጥር 7/2017 ዓ.ም

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገር ደረጃ የሚታዩና የሚጨበጡ ስራዎችን መስራቱን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዲሱ ሻንቆ ገለጹ፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ ሁለተኛውን የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ አካሂዷል።

ፓርቲው ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገር ደረጃ የሚታዩና የሚጨበጡ ስራዎችን የሰራ ስለመሆኑ ያነሱት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዲሱ ሻንቆ የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል ጀምሮ ፍትሃዊና እኩል ተጠቃሚ በማድረግ ሰፊ ስራዎች ተሰርቷልም ብለዋል።

ለዚህም ስራዎቹ ራሳቸው ህያው ምስክር እንደሆኑ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በፓርቲው ውስጥ ካሉ አመራሮችና አባላት ብዙ ስራዎች ይጠበቃሉ ብለዋል።

ፓርቲው በቀጣይ የጀመራቸውን ስራዎች ሌት ከቀን በትጋት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

በጽዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review