***********************
ብልፅግና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ተቃርኖዎችን የሚያስታርቅ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ብልፅግና ሚዛናዊነትን፣ አስተሳሳሪ ትርክትን እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልፅግናን መሰረት አድርጎ የተቋቋመ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግም ፤ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት በማቀፍ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
እውነተኛ የኅብረ ብሔራዊ ፓርቲ ሥርዓትን በመተግበርም የዜጎችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በፍትሃዊነት እና በዘላቂነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ከተለያዩ ሀገራት የመጡ እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄድ ነው።