ብልፅግና ፓርቲ እንደ ሀገር የተጀመረውን እድገት ለማፋጠን እየሰራ ነው – አቶ አደም ፋራህ

You are currently viewing ብልፅግና ፓርቲ እንደ ሀገር የተጀመረውን እድገት ለማፋጠን እየሰራ ነው – አቶ አደም ፋራህ

AMN – መጋቢት 24/2017

ብልፅግና ፓርቲ እንደ ሀገር የተጀመረውን እድገት ለማፋጠን እየሰራ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች መጋቢት 24ን ያከበሩ ሲሆን፤ ጎን ለጎንም ለፓርቲው ዋና ጽሕፈት ቤት አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ውጤታማ የምዘና ሥርዓትን መዘርጋትን ያለመ የስልጠና መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡

አቶ አደም ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ ግልፅና ተጨባጭ መስፈርቶች ላይ የተመሰረተ፣ ወቅታዊና ጥራት ያላቸው የምዘና መረጃዎችን በግብዓትነት የሚጠቀም፣ አሳታፊ፣ ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለማምጣት የሚረዳ የግብረ መልስ ሥርዓት ያለውና የቅሬታ ሥርዓትን ያካተተ ወጥ የምዘና ሂደት ለመዘርጋት በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ውጤታማ የምዘና ሥርዓትን በመዘርጋት እንደ ሀገር የተጀመረውን እድገት ለማፋጠን እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

ተልዕኮን፣ እቅድንና አፈፃፀምን ማዕከል ያደረገ ውጤታማ የምዘና ሥርዓት በስራ ላይ ማዋል፤ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የጀመርነውን ጉዞ ለማፋጠን ጉልህ ሚና አለው ማለታቸውን በብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review