ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሰነድነት መጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

You are currently viewing ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሰነድነት መጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

AMN – ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ ለኢትዮጵያ) ስርዓቶቻቸውን በማቀናጀት ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሰነድነት መጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመሆን ምዝገባ ከመያዝ ጀምሮ እስከ መሳፈር ድረስ ያለውን የመንገደኞች አገልግሎት ባዮ ሜትሪክ መረጃን በመጠቀም ይበልጥ ለማቀላጠፍ እንደሚሰራ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review