ብሔራዊ ጥቅም የሚመዘነው በግለሰብ ጥቅም ሳይሆን በጋራ ጥቅም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

You are currently viewing ብሔራዊ ጥቅም የሚመዘነው በግለሰብ ጥቅም ሳይሆን በጋራ ጥቅም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

AMN ግንቦት 28/2017

በኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት የዋጋ ግሽበት የተከሰተ ሲሆን ከለውጡ በፊት ብቻ ከአሥር ዓመታት በላይ ሳይቋረጥ መከሰቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ ትኩረት እና ጉዞን የሚፈትኑ ችግሮች ያጋጠሙ ሲሆን በተለይም የኮሮና ወረርሽኝና የዩክሬን ጦርነት ለአፍሪካ ድጋፍ የሚያደርጉ ሀገራትን ሀሳብ አስቀይሯል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በተለያዩ ኃይሎችም ሀገር ውስጥ ግጭት መፈጠሩ ተጨማሪ ችግር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የዋጋ ግሽበት ዓለም ዓቀፍ ችግር መሆኑንም አንስተዋል፡፡ በፈረንጆቹ 2020 በቱርክ 58 በመቶ ግሽበት ተከስቷል፡፡ ነገር ግን ቱርክ ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበች ሀገር ናት ብለዋል፡፡

ግብፅ 33 እንዲሁም አርጀንቲና ከ200 በላይ ግሽበት አስተናግደዋል፡፡ ችግሩ ዓለምን የናጠ በመሆኑ እንደ ሀገር ከዚህ ለማምለጥ በምዕራፍ የተከፋፈለ ጠንካራ ሥራ መሠራቱን አስታውቀዋል፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ የተሳሰረ ፕሮጀክት፣ የንግድ እንቅስቃሴ ፣ የመበደርና ብድር የመመለስ እንዲሁም ኤክስፖርትን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የነበረው መተሳሰር የሚቀይር እና የሚያፍታታ ውሳኔ ተወስኗል ነው ያሉት፡፡

በሁለተኛው የማንሰራራት ምዕራፍ ደግሞ ተቋም መገንባትና ፈጠራን ማከል ወሳኝነት ያላቸው በመሆኑ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review