ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውንና ታሪካቸውን ለተተኪ ትውልድ የሚያስተላልፉበት አትላስ/ፕሮፋይል/ ጥናት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተገለጸ

You are currently viewing ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውንና ታሪካቸውን ለተተኪ ትውልድ የሚያስተላልፉበት አትላስ/ፕሮፋይል/ ጥናት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተገለጸ

AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም

ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለተተኪ ትውልድ የሚያስተላልፉበት አትላስ/ፕሮፋይል/ ጥናት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተገለጸ፡፡

የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ምክር ቤት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም በሚያካሄደው አራተኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በበጀት ዓመቱ የያዛቸው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ከበደ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ዲሞክራሲ ዕውን እንዲሆንና ሕዝቡም ለውጡ ለምን አስፈለገ የሚለውን እንዲገነዘብ ጭምር የሕዝቦችን ጥያቄ በመመለስ በኩል ምክር ቤቱ ብሎም ቋሚ ኮሚቴው የሄደበትን ርቀት አድንቀው በቀጣይም ቋሚ ኮሚቴው ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ፍቅሬ አማን የቋሚ ኮሚቴው የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን፤ በበጀት ዓመቱ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለምክር ቤቱ ለሚቀርቡ የመዋቅር ጥያቄዎችም ሆኑ የማንነት አቤቱታዎች የአገራችን የብልጽግና ጉዞ ሊያፋጥን በሚችል መልኩ በጥናት ላይ በመመስረት ሕገ መንግሥታዊ መፍትሄ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም ለጠንካራ የሕዝቦች ትስስርና ለአስተማማኝ ሰላም ግንባታ አወንታዊ ሚና ያላቸው ጉዳዮችን በበጀት ዓመቱ በስፋት ለመስራት መታቀዱን gleTwale::

ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ቋንቋቸውንና ልምዳቸውን ለተተኪ ትውልድ የሚያስተላልፉበት እንዲሁም ከብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ብዥታዎችን የሚያጠራና ለሕዝቦች መቀራረብ የላቀ ሚና እንደሚኖረው የሚጠበቀው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እየተጠና የሚገኘውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አትላስ /ፕሮፋይል/ ጥናት ማፋጠንና ሌሎች የተለየ ትኩረት የሚፈልጉ ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች ሳይንሳዊ መፍትሄ እንዲያገኙ ማድረግ በበጀት ዓመቱ ከሚፈጸሙ ዐበይት ተግባራት መካከል እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ቋሚ ኮሚቴው በእነዚህና በሌሎች አንኳር ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ዕቅዱን ለምክር ቤት ይዞ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክር ቤቱ ባለፉት አጭር የለውጥ ዓመታት የሕዝቦችን እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ በቀድሞው ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ ለነበሩ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ምላሽ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review