ኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፉን የብዝሃ ህይወት ቀን ”ከተፈጥሮ ጋር መስማማት ለዘላቂ ልማት ” በሚል መሪ ሀሳብ ለ24ኛ ጊዜ ተከብሯል።
በመርሐ-ግብሩም ከኢንስቲትዩቱ የተውጣጡ ባለሙያዎችን ጨምሮ የግብርና ሚኒስቴር፣ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እና የሌሎች ተቋማት ባለሙያዎች እንዲሁም በዘርፉ ጥናትና ምርምር ያደረጉ አካላት ተገኝተዋል።
የብዝሃ ህይወትን ለማስጠበቅ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የሚያበረክተው ሚና ላቅ ያለ ስለመሆኑም በዚሁ መድረክ ተመላክቷል።
ተፈጥሮን በዘላቂነት መጠበቅ እና ዘለቄታው የተረጋገጠ የልማት ተግባር ለማከናወን ብዝሃ ህይወትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል።
በመድረኩ በዓሉን የሚመለከት የፓናል ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በኢንስቲትዩቱ በዐውደ-ርዕይ የቀረቡ የተለያዩ የብዝሃ ህይወት ዝርያዎችም ለጉብኝት ቀርበዋል።
በአይናለም አባይነህ