ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያን የድል ቀን አስመልክተው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አወጁ

You are currently viewing ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያን የድል ቀን አስመልክተው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አወጁ

AMN – ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከግንቦት 8 እስከ 10 የሚከበረዉን የሩሲያ የድል ቀንን አስመልክተው የዩክሬን ጦርነት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አውጀዋል።

ክሬምሊን የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጾ ዩክሬን ይህን አርአያ እንድትከተል አሳስቧል። ማንኛውም ጥሰቶች ከሩሲያ ኃይሎች “በቂ እና ውጤታማ ምላሽ” እንደሚሰጡባቸውም አስጠንቅቋል።

ይህ መግለጫ የወጣው ዩኤስ ሳምንቱን ለሩሲያ እና ለዩክሬን የሰላም ንግግሮች ወሳኝ ነው ባለበት ወቅት ነው። ቢቢሲ እንደዘገበዉ ባለፈው ተመሳሳይ የትንሳኤ የተኩስ አቁም ጦርነቱ የተወሰነ ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም ሁለቱም ወገኖች እርስበርስ ጥሰት ተፈፅሟል በማለት ሲወነጅሉ ነበር።

በሊያ ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review