ታላቁ ኢትዮ-ኢድ ኤክስፖና ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ

You are currently viewing ታላቁ ኢትዮ-ኢድ ኤክስፖና ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ

AMN – መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

ባዛሩ፣ በበዓላት ወቅት ማህበረሰቡ የሚፈልጋቸውን ምርቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ በማድረግ ገበያን በማረጋጋት ረገድ የጎላ ድርሻ አለው ተብሏል፡፡

ባዛሩን 3ኢ ኤቨንትስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር እና ቢላሉል ሃበሺ የልማትና የመረዳጃ ዕድር በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፤በረመዳን ጾም ወቅት በትክክለኛው መንገድ በመገብየት የአብሮነትና የጋራ እሴቶች ማጎልበት ይገባል ብለዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ነፊሳ አልማኻዲ፣ በዛሩ ሸማቾች የሚፈልጓቸውን ምርቶች በአንድ ቦታ ማግኘታቸው ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው፣ እንደዚህ ዓይነት ባዛሮች የሰዎችን መስተጋብር ያጠነክራሉ ብለዋል።

በኤክስፖው ላይ ከ150 በላይ የንግድ ኩባንያዎችን ለማስተናገድ ቦታ መዘጋጀቱን የገለጹት አዘጋጆቹ፣ እያንዳንዳቸው አልባሳት፣ የሥነ ጥበብ ሥራ፣ የቤት እቃ እና ዘርፈ ብዙ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ይሳተፉበታል ተብሏል።

ባዛሩ እስከ መጋቢት 21 የሚቆይ ሲሆን፣ ከጠዋት 3 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ማኅበረሰቡን እንደሚያስተናገድም ለማወቅ ተችሏል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review