ትራምፕ በአውሮፓ ኅብረት ላይ ለመጣል ያቀዱትን የ50 በመቶ ታሪፍ ቀነ ገደብ አራዘሙ

AMN – ግንቦት 18/2017 ዓ.ም

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአውሮፓ ኅብረት ላይ ለመጣል ያቀዱትን የ50 በመቶ ታሪፍ ቀነ ገደብ እስከ ፈረንጆቹ ሐምሌ 9 ድረስ አራዝመዋል፡፡

ትራምፕ የታሪፍ ትግበራውን ያራዘሙት ከአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ኃላፊ ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ጋር በስልክ ከተወያዩ በኃላ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኃላፊዋ ስልክ ደውለው በታሪፍ ትግበራው ላይ ጠንከር ያለ ድርድር ማድረግ እንደሚፈልጉ እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡

የታሪፍ ትግበራው ቀነ ገድብ እንዲራዘም ጥያቄ አቅርበውልኝ ፤ “እኔ ያንን ለማድረግ ተስማምቻለሁ” ብለዋል፡፡

ኃላፊዋ ከስልክ ውይይቱ በኋላ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ከትራምፕ ጋር “መልካም ቆይታ” ማድረጋቸውን ጠቁመው ፤ “ጥሩ ስምምነት” ላይ ለመድረስ እስከ ሐምሌ 9 ድረስ ተጨማሪ ቀን እንደሚያስፈልጋቸው ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 27 አባል ሀገራት ባሉት የአውሮፓ ኅብረት ላይ 50 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ መዛታቸው ይታወሳል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review