ትራምፕ 100ኛ የስልጣን ቀናቸውን ራሳቸውን በማወደስ እና ተቃዋሚዎቻቸውን በመተቸት አከበሩ

You are currently viewing ትራምፕ 100ኛ የስልጣን ቀናቸውን ራሳቸውን በማወደስ እና ተቃዋሚዎቻቸውን በመተቸት አከበሩ

AMN ሚያዚያ 22/2017 ዓ.ም

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸውን 100ኛ ቀን ሚቺጋን ላይ ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስል ሰልፍ አክብረዋል።

ትራምፕ የኢኮኖሚ ለውጥ እና የኢሚግሬሽን እርምጃዎችን አፅንዖት ሰጥተው ሲናገሩ የተደመጡ ሲሆን፣ ተወዳጅነታቸው እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳዩ አሉታዊ አስተያየቶችን ግን ውሸት ሲሉ አጣጥለዋል።

ህገ-ወጥ የድንበር ማቋረጦችን በመቀነስ ረገድ ስኬታማ መሆናቸውን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፣ ከኢንዱስትሪ መገፋፋት በኋላ በመኪና ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ የታሪፍ ቅናሽ መደረጉን አስታውቀዋል።

የትራምፕ ተቀናቃኝ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የ100 ቀናት አፈፃፀማቸውን “ግዙፍ ውድቀት” በማለት ገልፆታል፡፡

ጋላፕ የተባለው የሕዝብ አስተያት መሰብሰቢያ፣ ትራምፕ በ100 ቀናት የሥልጣን ቆይታቸው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከግማሽ በታች የሆነው ሕዝብ የሚደግፋቸው ብቸኛ መሪ ናቸው ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንቱ በኢኮኖሚ ትግል እና የዋጋ ንረት ላይ ከዲሞክራቲክ ብሄራዊ ኮሚቴ ትችት ቢሰነዘርባቸውም በሪፐብሊካን መራጮች መካከል አሁንም ጠንካራ ድጋፍ እንዳላቸው ዘገባው አመላክቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review