AMN – የካቲት 13/2017 ዓ.ም
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ከሜዳው ውጪ ወደ ቪላ ፓርክ አምርቶ የኡናይ ኤምሬውን አስቶንቪላን የገጠመው ሊቨርፑል ነጥብ ጥሏል፡፡
በመሀመድ ሳላህ ግብ ቀዳሚ መሆን ችሎ የነበረው ሊቨርፑል ዩሪ ቴሊማንስ እና ኦሊ ዋትኪንስ ለአሰቶን ቪላ አከታትሎ ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ጨዋታውን 2ለ1 እየመሩ ለዕረፍት ወጥተዋል።
ከዕረፍት መልስ አሌክስሳንደር አርኖልድ በ61ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ጨዋታው 2ለ2 አቻ በሆነ ውጤት ሊጠናቀቅ ችሏል።
ሊቨርፑል ነጥብ መጣሉን ተከትሎ ከተከታዪ አርሴናል በ10 ነጥብ የመራቅ እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
የደረጃ ሰንጠረዡን ሊቨርፑል በ61 ነጥብ 1ኛ ሆኖ ሲመራ አርሴናል በ53 ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
በጃዕፈር አህመድ