ቻይና የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቿን በተመለከተ በወጣ ሪፖርት ላይ አስተያየት እንደሌላት አስታወቀች

You are currently viewing ቻይና የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቿን በተመለከተ በወጣ ሪፖርት ላይ አስተያየት እንደሌላት አስታወቀች

AMN- ሰኔ 9/2017 ዓ.ም

ቻይና የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎቿን በተመለከተ አንድ የባለሙያዎች ቡድን ባወጣው ሪፖርት ላይ አስተያየት የላትም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉ ዣኩን፣ ቻይና በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ያለ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት መሆኗን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ቻይና የኒውክሌር አቅሟን ለብሔራዊ ደህንነት በሚያስፈልጋት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ በማስቀመጥ ራሷን የመከላከል ስትራቴጂን ስትከተል መቆየቷንም አንስተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ጉ ዣኩን አያይዘውም፣ ቻይና ከዚህ ውጪ በጦር መሣሪያ ውድድር ውስጥ አትሳተፍም ሲሉ መናገራቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

ዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን አዲሱን የጦር መሳሪያዎች ውድድር አስመልክቶ ባካሄደው ዓመታዊ የጦር መሳሪያ ቆጠራ፣ የቻይና የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ዓይነቶች 600 መድረሱን አመላክቷል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review