ቼልሲ የዩሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ አሸናፊ ሆነ

You are currently viewing ቼልሲ የዩሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ አሸናፊ ሆነ

AMN-ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

በፖላንድ ሮክሎው ስታዲየም የተደረገው የቼልሲ እና ሪያል ቤቲስ ጨዋታ በእንግሊዙ ክለብ 4ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻሉ የነበሩት ሪያል ቤቲሶች በአብዴ ኤዛልዙሊ ግብ ቀዳሚ መሆን ችለው ነበር።

በሁለተኛው አጋማሽ የሚጠበቅባቸውን ማድረግ የቻሉት ቼልሲዎች ግን አራት ግቦችን አስቆጥረዋል።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ ፣ ኒኮላስ ጃክሰን ፣ ጄደን ሳንቾ እና ሞይሰስ ካይሴዶ የቼልሲን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

ቼልሲ ድሉን ተከትሎ ቻምፒየንስ ሊግ ፣ ዩሮፓ ሊግ ፣ ኮንፍረንስ ሊግ እና ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን ያሸነፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review