ነዳጅ የደብቁ ማደያዎች ከገበያ እንዲወጡ ተደረገ

You are currently viewing ነዳጅ የደብቁ ማደያዎች ከገበያ እንዲወጡ ተደረገ

AMN- ሰኔ 15/2017 ዓ.ም

የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ሀሳብ ነዳጅ በደብቁ ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአዲስ አበባ ከ5 ሚሊየን ሊትር በላይ ነዳጅ ቢኖርም፣ ነደጅ የለም በማለት አገልግሎት ያቆሙ ማደያዎች መኖራቸው መረጋገጡን አብራርተዋል።

በተደረገው ክትትልና ማጣራትም፣ በቂ ነዳጅ እያላቸው አገልግሎት ያቆሙ ሁለት ማደያዎች ከግብይት እንዲወጡና ስራ አስኪያጆቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

ባምቢስ ኖክ እና መርካቶ ሀበሻ እርምጃ የተወሰደባቸው ማደያዎች መሆናቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፣ በነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ አለመኖሩን አረጋግጠዋል።

መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ ከነዳጅ ድጎማ መውጣቱን አስታውሰው፣ የነዳጅ ዋጋም በዓለም የነዳጅ ገበያ ብቻ ይወሰናል ብለዋል።

ከአሁን በኋላ በየወሩ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ እንደማይኖርም ሚንስተሩ ተናግረዋል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review