ኑክሌር በታጠቁ ሁለቱ ጎረቤት ሃገራት መካከል የተጀመረዉ የመልሶ ማጥቃትና እሰጣ ገባ በአካባቢዉ ከፍተኛ ዉጥረት መፍጠሩ ተነገረ

You are currently viewing ኑክሌር በታጠቁ ሁለቱ ጎረቤት ሃገራት መካከል የተጀመረዉ የመልሶ ማጥቃትና እሰጣ ገባ በአካባቢዉ ከፍተኛ ዉጥረት መፍጠሩ ተነገረ

ኑክሌር በታጠቁ ሁለቱ ጎረቤት ሃገራት መካከል የተጀመረዉ የመልሶ ማጥቃትና እሰጣ ገባ በአካባቢዉ ከፍተኛ ዉጥረት መፍጠሩ ተነገረ

AMN – ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም

ኑክሌር በታጠቁ ሁለቱ ጎረቤት ሃገራት በህንድና ፖኪስታን መካከል የተጀመረዉ የመልሶ ማጥቃትና እሰጣ ገባ በአካባቢዉ ከፍተኛ ዉጥረት መፍጠሩ እየተነገረ ነዉ፡፡

ህንድ በፖኪስታን ላይ የፈጸመችዉን የሚሳኤል ጥቃት ተከትሎ ፓኪስታን አምስት የህንድ የጦር አውሮፕላኖችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ መጣሏን የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ህንድ በፓኪስታን ላይ ባደረሰችዉ ጥቃት ስምንት ሰዎች ሲሞቱ 35 ቆስለዋል፡፡

የፓኪስታን የመከላከያ ሚኒስትር ካዋጃ አሲፍ በአጸፋ እርምጃዉ አምስት የህንድ የጦር አውሮፕላኖች ተመትተዉ መዉደቃቸዉን ለብሉምበርግ ተናግረዋል፡፡

ህንድ ጸብ አጫሪነቷን ካቆመች ለመነጋገር ዝግጁ ነን፤ ሁኔታዉ እንዲባባስ አንፈልግም ነገር ግን ህንድ ጸብ አጫሪነቷን ካላቆመች ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ የፓኪስታን የመከላከያ ሚኒስትር ካዋጃ አሲፍ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡

የፓኪስታን ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሌተናል ጄኔራል አህመድ ሻሪፍ ቻውድሪ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ከሆነ፣ ፓኪስታን አምስት የህንድ የጦር አውሮፕላኖችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ ጥላለች፡፡

የህንድ መንግስት የመረጃ ምንጮች ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንዳረጋገጡት ከሆነ ህንድ በምታስተዳድረዉ የካሽሚር ግዛት ውስጥ ሶስት ተዋጊ ጄቶች ተከስክሰዋል።

ከዚሁ እሰጣ ገባ ጋር በተያያዘ ህንድ ‘ኦፕሬሽን ሲንዶር’ የተባለ የተኩስ ልዉዉጥ በፖኪስታን ላይ ማካሄድ መጀመሯን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ህንድ በፖኪስታንና ፖኪስታን በምታስተዳድራቸዉ የካሽሚር ግዛቶች በጀመረችዉ ኦፕሬሽን ወታደራዊ ኢላማዎች መመታታቸዉ ተጠቅሷል፡፡

ኑክሌር በታጠቁ ሁለቱ ጎረቤት ሃገራት መካከል የተጀመረዉ የመልሶ ማጥቃትና እሰጣ ገባ በአካባቢዉ ከፍተኛ ዉጥረት መፍጠሩን አልጀዚራ በዘገባዉ አመላክቷል፡፡

የህንድ ወታደራዊ አዛዦች በበኩላቸዉ፣ በሽብርተኞች መሰረት ልማት ላይ እርምጃ ከመዉሰድ ዉጪ የፖኪስታን ወታደራዊ ተቋማት ኢላማ አልተደረጉም ብለዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review