ጎንደር ከተማን ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለመመለስ ያለመ መሆኑ የተነገረለት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

You are currently viewing ጎንደር ከተማን ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለመመለስ ያለመ መሆኑ የተነገረለት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

AMN – ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም

ጎንደር ከተማን ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለመመለስ ያለመ መሆኑ የተነገረለት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡

“ኑ ጎንደርን እንሞሽር” የተሰኘው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል እንደሚካሄድ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው አስታውቀዋል።

የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብሩን በተመለከት መግለጫ የሰጡት አቶ ቻላቸው፤ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብሩ ጎንደርን ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለመመለስ ያለመ ነው ብለዋል።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብሩ መላው ኢትዮጵያዊያን ፣በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የሚገኙ የጎንደር ተወላጆች ፣ የተለያዩ የሀገራት ኢምባሲዎችና ተቋማት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review