ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ ኢትዮጵያ አባል ለመሆን ያቀረበችውን ጥያቄ ተቀበለ

You are currently viewing ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ ኢትዮጵያ አባል ለመሆን ያቀረበችውን ጥያቄ ተቀበለ

AMN- ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም

የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን ለመቀላቀል ያቀረበችውን ጥያቄ መቀበሉን አስታወቀ።

ባንኩ ኢትዮጵያ አባል ለመሆን የሚያስችላትን የድርድር ሂደት እንድትጀምር ጋብዟል።

ይህ ለኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ትልቅ ስኬት የሚባል መሆኑን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው በመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም ከባንኩ ፕሬዝዳንት ዲልማ ሩሴፍ ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።

በውይይቱም ኢትዮጵያ ለባለብዙ ወገን የፋይናንስ ትብብር እና ከባንኩ ጋር በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ እንደሆነች መግለጿን ኤምባሲው በመረጃው አስታውሷል።

ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ (በቀድሞ አጠራሩ የብሪክስ ልማት ባንክ) በብሪክስ አባል ሀገራት እ.አ.አ በ2014 ተቋቁሞ ከአንድ ዓመት በኋላ በ2015 ወደ ስራ መግባቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review