ጠፈርተኞች በተለያዩ ጊዜያት በህዋ ላይ በሚኖራቸው ቆይታ ከሚጠቀሟቸው ምግቦች እና ፈሳሽ ነገሮች የሚገኙ ተርፈ ምርቶችን ፣ ፍሳሽ እና ደረቅ ቆሻሻዎችን በማድቀቅ፣ በማቃጠል አልያም ወደ መሬት ይዞ በመመለስ በተለመደው መንገድ ያስወግዳሉ።
ናሳ ይህን አካሄድ ለመቀየር እና የጠፈር ቆሻሻ ወደ መሬት ሳይመለስ እዛው እያለ ጥቅም ላይ ለማዋል እቅድ ይዟል።
እቅዱን ሊያሳካለት የሚችል ቴክኖሎጂ ለሚፈጥር ሰው ደግሞ 3 ሚሊዮን ዶላር አዘጋጅቷል።
ናሳ አወዳድሮ አሸናፊ ለሚሆን አካል ነው ያዘጋጀውን ሽልማት የሚያበረክተው ሲል ዩፒአይ አስነብቧል።
በአሁኑ ሰዓት 96 ከረጢት ሰው ሰራሽ ቆሻሻ በጠፈር ላይ ተከማችቶ ይገኛል ።
በማሬ ቃጦ