አሜሪካ አዲስ ታሪፍ ከመጣሏ በፊት ፕሬዚዳንት ሺ- ጂንፒንግ ከ40 በላይ ታላላቅ የውጪ የንግድ ተቋማት መሪዎችን አወያዩ

You are currently viewing አሜሪካ አዲስ ታሪፍ ከመጣሏ በፊት ፕሬዚዳንት ሺ- ጂንፒንግ ከ40 በላይ ታላላቅ የውጪ የንግድ ተቋማት መሪዎችን አወያዩ

AMN – መጋቢት 20 /2017 ዓ.ም

ፕሬዚዳንት ሺ- ጂንፒንግ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲስ የ25 በመቶ ታሪፍ ከመጣላቸው በፊት ከ40 በላይ ታላላቅ የውጪ የንግድ ተቋማት መሪዎችን ማወያየታቸው ተገለጸ።

የቻይናው መሪ ሺ-ጂንፒንግ ቻይና ቤጂንግ በሚገኘው ታላቁ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከአለም አቀፍ የንግድ ተቋማት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ስብሰባ ላይ የ86 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተወካዮች መሳተፋቸዉ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ- ጂንፒንግ ከአሜሪካ ጋር እየተቀጣጠለ ከመጣው የንግድ ጦርነት ጋር በተያያዘ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ትራምፕ የ25 በመቶ ተጨማሪ ታሪፍ ለመጣል በሚቋምጡበት በዚህ ወቅት የቻይናው ፕሬዚዳንት ቻይና ከአሜሪካ ጋራ ዘላቂ እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ እንደምትከተል አስታዉቀዋል።

ሺ- ጂንፒንግ “ቻይና ሁሌም ምቹ፣ አስተማማኝ እና ተስፋ ሰጭ የውጭ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆና ቆይታለች፣አሁንም ትቀጥላለች” ሲሉ መናገራቸዉን ሲኤን ኤንና ዢንዋን ዘግበዋል።

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም የውጭ ኩባንያዎች ለቻይና ገቢና ወጪ ንግድ አንድ ሶስተኛውን እንዲሁም ከታክስ ገቢዋ ደግሞ አንድ ሠባተኛውን ድርሻ የሚያበረክቱ መሆናቸዉን አብራርተዋል፡፡

ከ30 ሚሊዮን ለሚልቁ ዜጎቿ የስራ እድል መፍጠራቸውንም እንዲሁ፡፡

በዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ቻይና 20 በመቶ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ማስመዝገቧን የሃገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

ቻይና በአፀፋው በተመረጡት የአሜሪካ ምርቶች ላይ እስከ 15 በመቶ የሚደርስ የግብርና እና የኢነርጂ ምርቶች ላይ ቀረጥ የጣለች ሲሆን በጥሬ ዕቃዎች ላይ አዲስ የኤክስፖርት ቁጥጥሮችን እንደምታደርግ ማስታወቋን ሲኤን ኤን ዘግቧል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review