
AMN – ግንቦት 6/2017 ዓ.ም
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያ ቀን ጉንኝታቸዉ ከልዑል አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር የተወያዩ ሲሆን የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።
ሳውዲ አረቢያ 600 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ በዩናይትድ ስቴትስ ለማፍሰስ የገባችው ቃል አካል የሆነውን የ142 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነትን ሁለቱ ሃገራት መፈራረማቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
ትራምፕ በሪያድ በተካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ለሶሪያ ታላቅነት እድል የምንሰጥበት ጊዜ አሁን ነው በማለት አሜሪካ በሀገሪቱ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንደምታነሳ አስታውቀዋል።
የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አል-ሺባኒ የአሜሪካ ማዕቀብ መነሳት ሀገራቸውን መልሶ ለመገንባት አዲስ ጅማሮ መሆኑን ተናግረዋል።
የትራምፕ የባህረ ሰላጤው ክልል የአራት ቀናት ጉብኝት የቀጠለ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ዛሬ በሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ በሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ እና ባህረ ሰላጤው ትብብር ምክር ቤት አባላት ጉባኤ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎንም ከሶሪያው ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ ጋር እንደሚገናኙ እየተነገረ ነዉ፡፡
ሐሙስ ዕለት ወደ ተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከማቅናታቸው በፊት ረቡዕ ወደ ኳታር እንደሚጓዙ ዘገባው አካቷል።
በሊያት ካሳሁን