አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ጦርነቱን ለማርገብ መስማማታቸው ተገለጸ

You are currently viewing አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ጦርነቱን ለማርገብ መስማማታቸው ተገለጸ

AMN- ሰኔ 4/2017 ዓ.ም

አሜሪካ እና ቻይና በንግድ ዙሪያ በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት ለማርገብ በለንደን ለሁለት ቀናት ከተነጋገሩ በኋላ በንግድ ማዕቀፍ ላይ ተስማምተዋል።

የሁለቱ ሀገራት ተደራዳሪዎች ስምምነቱ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ለቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ቀርቦ ይፀድቃል ብለዋል።

ዋሽንግተን እና ቤጂንግ በጄኔቫ ባደረጉት ውይይት አብዛኛውን የታሪፍ ጭማሪ ለ90 ቀናት ያዝ ለማድረግ ከተስማሙ ከአንድ ወር በኋላ የተካሄደው የለንደኑ ድርድርም፣ ዝርዝር ሁኔታው ግልፅ ባይደረግም፣ በንግድ ማዕቀፍ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ትናንት ይፋ ተደርጓል።

የአሜሪካ የንግድ ሚኒስትር ሃዋርድ ሉትኒክ፣ ሁለቱም ወገኖች የጄኔቫን ስምምነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የዓለም ግዙፍ ምጣኔ ሀብት ባለቤት የሆኑት ሁለቱ ሀገራት ከገቡበት ቅርቃር ለመውጣት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውንም ገልጸዋል።

ሉትኒክ አያይዘውም፣ ስምምነት የተደረሰባቸው የንግድ ማዕቀፎች፣ ሁለቱም ፕሬዚዳንቶች ፍቃዳቸውን ከሰጡ በኋላ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ማንሳታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review