አሜሪካ እና እስያ በካይ ጋዝ በመልቀቅ ትልቅ ድርሻ እያበረከቱ ነው፦ ሪፖርት

You are currently viewing አሜሪካ እና እስያ በካይ ጋዝ በመልቀቅ ትልቅ ድርሻ እያበረከቱ ነው፦ ሪፖርት

AMN – ኅዳር 07/2017 ዓ.ም

አሜሪካ እና እስያ ከፍተኛ የሆነ በካይ ጋዞችን በመልቀቅ ለአየር ንብረት ለውጥ ችግር ትልቅ ድርሻ እንደሚወስዱ በኮፕ 29 ጉባኤ ላይ የቀረበ ሪፖርት አመለከተ፡፡

ከሰሞኑ ሲካሄድ በቆየው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) ላይ የቀረበ መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ በእስያ ካሉ ከተሞች ሻንጋይ 256 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በካይ ጋዝ በመልቀቅ ኮሎምቢያ እና ኖርዌይን ትቀድማለች፡፡

ኒውዮርክ ከተማ 160 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እና ሂዩስተን 150 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በካይ በካይ ጋዝ በመልቀቅ በዓለም ደረጃ በካይ ጋዝ በመልቀቅ ከሚታወቁ 50 ሀገራት ተርታ ተሰልፈዋል፡፡

ቻይና፣ ሕንድ፣ ኢራን፣ ኢንዶኔዥያ እና ሩሲያ ደግሞ ከፈረንጆቹ 2022 እስከ 2023 ባሉት ዓመታት የልቀት መጠናቸው ጨምሮ እንደነበር መረጃው አመልክቷል፡፡ በአንጻሩ ቬንዙዌላ፣ ጃፓን፣ ጀርመን እና እንግሊዝ በነዚህ ወቅቶች የብክለት መጠናቸው ቀንሶ ነበር ተብሏል፡፡

በኮፕ 29 ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያዛቡ ችግሮችን ለመከላከል የሚስችሉ በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በጉባኤው ላይ በአንድ ገለልተኛ አካል የቀረበ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ችግሩን ለመከላከል ሀገራት በ2030 እስከ 6 ትሪሊዮን ዶላር ለዚሁ ዓላማ መዋል አለበት ማለቱን አፍሪካ ኒውስ ነው ያስነበበው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review