አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት እንድትወጣ መወሰኑን ተከትሎ ኬንያ ጊዜ ለማይሰጡ የጤና ችግሮች ህክምና ዝግጅት ማድረግ መጀመሯን አስታወቀች

You are currently viewing አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት እንድትወጣ መወሰኑን ተከትሎ ኬንያ ጊዜ ለማይሰጡ የጤና ችግሮች ህክምና ዝግጅት ማድረግ መጀመሯን አስታወቀች

AMN- ጥር 21/2017

ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት እንድትወጣ መወሰናቸውን ተከትሎ ኬንያ ጊዜ ለማይሰጡ የጤና ችግሮች ህክምና ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ መጀመሯን አስታውቃለች፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጥር 12 ቀን 2017 የመጀመሪያ የስራ ቀናቸው ሁሉም የውጭ ዕርዳታዎች ለ90 ቀናት እንዲታገዱ ፈርመዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሀገራቸው ከአለም አቀፍ ጤና ድርጅት እንድትወጣ ማገዳቸውን ተከትሎ ኬንያ የኤችአይቪ/ኤድስ ህክምና እና መከላከያ መርሃ ግብሮች እንደማይስተጓጎል በሀገሪቱ መንግስት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኩል ለህዝቧ አረጋግጣለ።

የጤና ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ፓትሪክ አሞፅ ዛሬ ለሚዲያ በሰጡበት መግለጫ ፕሬዝዳንቱ በውሳኔያቸው የሚጸኑ ከሆነ ችግሩን ለመቋቋም ከሌሎች የልማት አጋሮች ጋር በመሆን እንደሚሰሩ አስታውቀዋል ፡፡

የልማት አጋሮቹ የህክምና መስተጓጎልን እንዳይኖር በሀገር ውስጥ መድሃኒንቶች ማምረት ላይ ኢንቨስት እንዲያደረጉም ይሰራል ብለዋል።

በኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎች የነፍስ አድን መድሀኒት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሚኒስቴሩ ክልላዊ ትብብር እና አማራጭ የጤና ፋይናንስ ዘዴዎችን እያጠናከረ መሆኑን አሞፅ ገልፀዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው “ለኤችአይቪ መከላከል ፕሮግራሞች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ማቆም ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ለበሽታ እና ለሞት ሊያጋልጥ እና በማኅበረሰብ እና አገራት ውስጥ ስርጭቱን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ያዳክማል ብሏል።

እንደነዚህ ያሉት እርምጃዎች ዓለምን ወደ 1980 ዎቹ እና 1990 ዎቹ ሊመልሱ እንደሚችሉና ይህም በአሜሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞትና ለአሰቃቂ ችግር ሊዳርግ እንደሚችል ድርጅቱን ጠቅሶ የኬንያው K24 Digital ዘግቧል።

በቶለሳ መብራቴ

All reactions:

1616

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review