AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የምሥራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ተጠሪ ዳይሬክተር ፍራንዝ ሴልስቲን ጋር በፍልሰት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሁለቱ ወገኖች ባደረጉት ውይይት በፍልሰት እና ተያያዥ ጉዳዮች ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል መስማማታቸው ተመላክቷል፡፡