AMN – ጥር 13/2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኔዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ስቲጅን ጃንሰን ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በሁለትዮሽ ትብብር፣በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ያተኮረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ የኔዘርላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እያደረጉት ያለው ተሳትፎ ተምሳሌታዊ ፋይዳ ገልጸው ፥ በመተግበር ላይ ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠሩ ዕድሎችን በስፋት እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል ።
የኔዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ስቲጅን ጃንሰን ኢትዮጵያ ቀጣናውን ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት አድንቀው ኔዘርላንድስ ያላትን ድጋፍ ገልጸዋል።