AMN-የካቲት 13/2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከእንግሊዝ የቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አሊሰን ብላክበርን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ፍላጎቶች ዙሪያ የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮች ላይ መክረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው እና ልዩ መልክተኛዋ በተለይ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በምጣኔ ሐብት ትስስር፣ በፖለቲካ ምክክር እና በሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ አማካኝነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮችም መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።