AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከዓለም አቀፍ የፍልሰት ፖሊሲ ልማት ማዕከል ኃላፊ ሞኒካ ዛኔቴ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ፣ በፍልሰት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚቻልባቸውን አማራጮች መፈለግ ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።
በተለይም ዓለም አቀፍ የፍልሰት ፖሊሲ ልማት ማዕከል በአዲስ አበባ ቢሮ በሚከፍትበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።