የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማር ጋር ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ፥ በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ብርሃኑ÷ በሀገሪቱ በነበራቸው ቆይታ ከሚኒስቴሩ ጋር ተቀራርቦ በመስራት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ መቻላቸውን መግለጻቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡