አርሰናል ለብሩኖ ጉማሬሽ 70ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ማቅረቡ ተገለጸ

You are currently viewing አርሰናል ለብሩኖ ጉማሬሽ 70ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ማቅረቡ ተገለጸ

AMN-መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም

አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ዓመታት 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወቅ ነው፡፡

መድፈኞቹ አሁንም በመሪው ሊቨርፑል በ12 ነጥቦች ተበልጠው ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ክለቡ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ከአስራ አራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሩብ ፍፃሜን ሲያሳካ በወሳኙ ጨዋታም ከሪያል ማድሪድ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡

የማይክል አርቴታው ቡድን ፕሪምየር ሊጉን ጨምሮ በታላላቅ ውድድሮች ለማሸነፍ ግን አዳዲስ ተጨዋቾችን በማስፈረም ራሱን ማጠናከር እንዳለበት ይገለፃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቡድኑ በመጪው የክረምት የዝውውር መስኮት ሊያስፈርማቸው እንደሚችል ከሚጠበቁት ተጨዋቾች ቀዳሚው እና አንዱ የኒውካስትሉ አማካኝ ብሩኖ ጉማሬሽ መሆኑን ፕላኔት ስፖርት ዘግቧል፡፡

አርሰናል አማካኙን ለማዘዋወር 70 ሚሊየን ፓውንድ ማቅረቡም ታውቋል፡፡

በማጂፓይሶቹ በኩል ስለ ዝውውሩ የተባለ ነገር ባይኖርም ተጨዋቹ ወደ ለንደን የማቅናት ፍላጎት እንዳለው ይነገራል፡፡

የኤዲሃው ቡድን ከ70 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በካራባኦ ዋንጫ አሸናፊ እንዲሁም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካከሪ እንዲሆን በማድረግ ሂደት የብራዚላዊው ጉማሬሽ ሚና ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

በፈረንጆቹ 2022 ከሊዮን ለኒውካስትል ዩናይትድ ፊርማውን ያኖረ ሲሆን፣ 114 ጨዋታዎች አድርጎ 19 ጎሎች ማስቆጠር ችሏል፡፡

በበላይነህ ይልማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review