አርሰናል የሁለት ታዳጊ ተጨዋቾቹን ውል ለማራዘም መቃረቡ ተሰማ

You are currently viewing አርሰናል የሁለት ታዳጊ ተጨዋቾቹን ውል ለማራዘም መቃረቡ ተሰማ

AMN -ሚያዝያ1/2017 ዓ.ም

የሰሜን ለንደኑ አርሰናል የኢታን ንዋኔሪና ሊዊስ ስኬሊን ውል ለማራዘም ንግግር መጀመሩ ታወቀ፡፡ ከቀናት በፊት አንድሬ በርታን ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አድርጎ የቀጠረው አርሰናል ውላቸው የተገባደዱ ተጨዋቾችን ማነጋገር ጀምሯል፡፡

ሁለቱ ታዳጊዎች ደግሞ ቅድሚያውን መውሰዳቸው ተሰምቷል፡፡ የ18 ዓመቱ ኢታን ንዋኔሪ ከመድፈኞቹ ጋር ያለው ውል በሚቀጥለው የውድድር ዓመት መጨረሻ ይጠናቀቃል፡፡

ክለቡ ከንዋኔሪ ተወካዮች ጋር ተገናኝቶ ንግግር ማድረጉን እና ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸው ታውቋል፡፡ በዚህ ዓመት 31 ጨዋታዎችን ለአርሰናል ያደረገው ንዋኔሪ፣ እንደ ቡካዮ ሳካ፣ ካይ ሃቨርዝ፣ ጋብሬል ማሪቲኔሊና ጋብሬል ጀሱስን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ሲጎዱ ክፍተታቸውን በመሙላት ሲወደስ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የመስመር ተከላካዩ ሊዊስ ስኬሊም ሌላው ንግግር የጀመረ ታዳጊ ነው ተብሏል፡፡ የቶማስ ቱኼል ቀዳሚ ተመራጭ ሆኖ ለብሄራዊ ቡድን ግልጋሎት የሰጠው ስኬሊ በአርሰናል ለረጅም ዓመት የሚያቆየውን ውል ለመፈራረም መቃረቡ ተነግሯል፡፡

አንድሬ በርታ ከነዚህ ወጣት ተጨዋቾች በተጨማሪ የቡካዮ ሳካ፣ ጋብሬል ማጋሌሽና ዊሊያም ሳሊባን ጨምሮ የበርካታ ተጨዋቾችን ውል የማራዘም ተደራራቢ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማስታወስ የዘገበው ቢቢሲ ስፖርት ነው፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review