አሸባሪዉ ኦነግ ሸኔን የመደምሰስ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ

You are currently viewing አሸባሪዉ ኦነግ ሸኔን የመደምሰስ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ

AMN- ህዳር 11/2017 ዓ.ም

በቄለም ወለጋ ዞን በአንፍሎ ወረዳ በምዕራብ ሸዋ ዞን አማያ ወረዳ ያበሎ ቀበሌ በሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ቡድን ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አመራሮች ገልፀዋል።

በማዕከላዊ ዕዝ የዋልያ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደሳለኝ ሙላዉ ሰላምን ማደፍረስና ንፁሃንን መጨፍጨፍ አላማዉ አድርጎ የተነሳዉ አሸባሪ ቡድን የሠራዊቱን ምት መቋቋም ሲያቅተዉ የጣዕረ-ሞት እድሜዉን ለማራዘም በየጫካዉ እየተሹለከለከ ለመሸሸግ ቢሞክርም ሠራዊቱ እግር በእግር እየተከታተለ መምታት መቻሉን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የማዕከላዊ ዕዝ ክፍለጦር በምዕራብ ሸዋ ዞን አማያ ወረዳ ያበሎ ቀበሌ የህዝብን ሰላም መንሳት ዓላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የሽብር ቡድኑ ሸኔ በሠራዊቱ እና በህብረተሰቡ የጋራ ትብብር ፍላጎቱን ማምከን ተችሏል።

የዘረፈውን ተሽከርካሪና ሞተር ሳይክል እንዲሁም የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ዳግም ፈይሳ መናገራቸውን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review