አትሌት ሰለሞን ባረጋ በማንችስተር የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አሸነፈ

AMN-ግንቦት 10/2017 ዓ.ም

በማንቸስተር በተደረገው 10 ኪሎ ሜትር የወንዶች ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸንፏል።

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ27:49 በሆነ ስዓት ውድድሩን በአንደኝነት ማሸነፍ ችሏል።

በውድድሩ ላይ የተሳተፈው አትሌት ሞስነት ገረመው በ28:21 አራተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቁን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review