ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር መነጋገራቸዉን ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ የኢዩቤልዩ ቤተ መንግሥትን ከጎበኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተነጋግረናል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ግንባታ ተገቢውን አስተዋጽዖ እንድታበረክት መንግሥት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚወጣ ገልጬላቸዋለሁ።
አዲስ ለተመደቡት ብጹአን አባቶች መልካም የሥራ ዘመን ተመኝቻለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡