AMN- የካቲት 16/2017 ዓ.ም
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለ8ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የቱርኩ ኤኬ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ከብልፅግና ፓርቲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ለመሥራት በቅርቡ የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመው ኤኬ ፓርቲ፤ በዛሬው እለት ጠቅላላ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።
ፓርቲው ከምስረታው እኤአ ከ2001 ጀምሮ 2 አስርት ዓመታት በተሻገረው የአመራርነት ዘመን በሀገረ ቱርክ ላስመዘገባቸው ድሎች፣በኤኬ ፓርቲ መሪነት ለተመዘገቡ ስኬቶች ብልፅግና ፓርቲ ያለውን አድናቆት መግለጻቸውን ከፓርቲው ማኀበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።