አቶ አደም ፋራህ ከሩዋንዳው አምባሳደር ቻርለስ ካራምባ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing አቶ አደም ፋራህ ከሩዋንዳው አምባሳደር ቻርለስ ካራምባ ጋር ተወያዩ

AMN – ጥር 14/2017 ዓ.ም

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ከሩዋንዳው አምባሳደር ቻርለስ ካራምባ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ አደም ፋራህ አምባሳደር ቻርለስን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መንግስታዊ እንዲሁም ፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል።

በውይይታቸው የፓርቲ ለፓርቲ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ውይይቶችን አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በኮሪደር ልማት ፣በአረንጓዴ አሻራ ፣በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲሁም በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል የጀመረቻቸው ስራዎች አበረታች መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል።

አቶ አደም ፋራህ፥ ብልፅግና ፓርቲ በአንደኛው መደበኛ ጉባኤ ለመተግበር ቃል የገባቸው ጉዳዮች በአግባቡ እየተተገበሩ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም በየዘርፉ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው፥

በሁለተኛው የፓርቲው መደበኛ ጉባኤ የተገኙ ስኬቶችን የሚያስቀጥሉ ውሳኔዎች እንደሚጠበቁ አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች እንዲሁም ቀጣይ ግቦችና ራዕዮች ላይም ገለጻ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ቻርለሰስ ካራምባ በበኩላቸው፥ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እንድንሳተፍ በመጋበዛችን እናመሰግናለን ብለዋል።

በጉባኤው ላይ የሚሳተፍ የልዑክ ቡድን ከሩዋንዳው ገዢ ፓርቲ RPF ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ ሲሆን የአገራቱን ግንኙነት የሚያጠናክሩ የሁለትዮሽ ውይይቶች እንደሚደረጉም መነሳቱን ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review