አቶ አደም ፋራህ የቱርኩ አክ ፓርቲ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አንካራ ገቡ

You are currently viewing አቶ አደም ፋራህ የቱርኩ አክ ፓርቲ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አንካራ ገቡ

AMN – የካቲት 15/2017 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የቱርኩ አክ ፓርቲ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቱርክ አንካራ ገብተዋል።

አቶ አደም፣ አንካራ ሲደርሱ የአክ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና በቱርክ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሀመድን ጨምሮ የኤምባሲው አመራሮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከብልፅግና ፓርቲ ማኀበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቱርኩ አክ ፓርቲ ከፊታችን ፌብሩዋሪ 23 ጀምሮ ጠቅላላ ጉባዔውን እንደሚያካሂድም ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review