ሚዲያው አዲስ አበባ ያስመዘገበችውን ሁለንተናዊ ለውጥ አጉልቶ በማውጣት እንደ ሚዲያ የተወጣው ሀላፊነት የሚያስመሰግነው መሆኑን የተቋሙ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለፁ።
በለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኘውን አዲስ አበባ ከተማን በየቀኑ የምታስመዘግበውን ለውጥ በማነፍነፍ አዳዲስ መረጃዎችን እያደረሰ የሚገኝ ሚዲያ ነውም ብለዋል።
አቶ ሞገስ “የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሃገራዊ መግባባት ካስማ፤ የትውልድ ግንባታ መሰረት ነው” በሚል መሪ ቃል ከተቋሙ ባለሙያዎች እና የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው።

ሚዲያና ኮሚኒኬሸን ለሀገር ግንባታ ተቀናጅተው ከፍተኛ የሆነ አወንታዊ የድርሻ ማበርከታቸውን ጠቅሰው በዚህ ረገድ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በሚዲያው ኢንዱስትሪ በአርዓያነት የሚወሳ ተግባር ማከናወኑ የሚያኮራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ሚዲያው የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ እንዲያስቀጥልም ነው የተቋሙ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢው አቶ ሞገስ ባልቻ ያሳሰቡት።
በማሬ ቃጦ