AMN- መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
ተመራጭ ሜትሮፖሊታን ሚዲያ ለመሆን እየተጋ የሚገኘው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የጀመራቸውን የህዝብ አገልጋይነት ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
የኤኤምኤን የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጥራት ፣ ፍጥነት፣ ፈጠራ እና የሀሳብ ነፃነትን አማክሎ የከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት ከህዝብ ዓይን እና ጆሮ በቀዳሚነት እያደረሰ የሚገኝ ሚዲያ መሆኑ ተመላክቷል።
በምርመራ፣በዶክመንተሪ፣ በዜና እና ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም የመዝናኛ ዝግጅቶቹም ተመራጭቱን ያሳደጉ መሆናቸው ተገልጿል።
በኤኤምኤን እና አዲስ በጀመረው ኤኤምኤን ፕላስ የቋንቋዎች ቻናል፣ በሬዲዮ፣ በዲጂታል እና ህትመት ዘርፍ አድማጭ ተመልካቹን 24/7 በማገልገል ከህዝብ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ እንደሚሠራ ተመላክቷል።

ሚዲያው ብልሹ አሰራሮች እንዲታረሙ እና የመንግስት እና ህዝብ ሀብት ለታለመለት ዓላማ መዋሉን የሚከታተልባቸው የዋርካ፣ አገልጋዩ እና ጠረጴዛ በተሰኙ ዝግጅቶቹ ውጤት ማምጣት መቻሉን ሚዲያው የ6 ወር ሪፖርቱን ለውይይት ባቀረበበት መድረክ ላይ ተገልጿል።
በምርመራ ዘገባ ሥራዎቹም ይበል የሚያሰኝ ተግባር አከናውኗል።
በሚዲያ ቴክኖሎጂ ረገድ ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ሥራ ላይ በማዋል የቀጥታ ስርጭት ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ተደራሽነቱን ለማስፋትም በዲጂታል፣በህትመት፣በዜና ዝግጅት ሥራዎቹ ማሻሻያዎችን በማድረግ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ መሆኑን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የተጣለበትን ሀላፊነት ከመወጣት ጎን ለጎን በተለያዩ በጎ አድራጎት ተቋማት ተገኝቶ የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሰብዓዊ ተግባራት ማከናወኑ ተነግሯል።
ባለፉት 6 ወራት በሁሉም ዘርፎች 96 ነጥብ 6 በመቶ አፈፃፀም ማስመዝገብ የቻለው ኤኤምኤን ከመንግስትና ከሌሎች ተቋማት ለጠንካራ አፈፃፀሙ እውቅና ተሰጥቶታል።
በማሬ ቃጦ