አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አከበረ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አከበረ

AMN – ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን በተቋሙ ቅጥር ግቢ አክብሯል፡፡

17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ ይገኛል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክም ቀኑን በማስመልከት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሣሁን ጎንፋን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት እና ሠራተኞች በተገኙበት ቀኑን አክብሯል።

በተቋሙ በምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማዕረግ የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ዳዲ በመርሐ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሰንደቅ ዓላማችን የነፃነት፣ የድላችን እና የሉዓላዊነታችን መገለጫ ነው ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review