AMN-መጋቢት 05/2017 ዓ.ም
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 72ኛ የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብ ስነ-ስርዓትን በመከታተል ተገቢዉን ሸፋን በመስጠት ለሰራው ስራ እውቅና አግኝቷል።
በ72ኛዉ የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብ ላይ በመሳተፍ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ሲሰጡ የነበሩ ለተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያ ተቋማት በዛሬው ዕለት እዉቅና ተሰጥቷቸዋል።
በአዲስ አበባ በተካሄደዉ የእዉቅና መርሃ ግብር ላይ መልእክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ፎረም ከተመሰረተ የተደራጀ ዉጤታማ የሚዲያ ስራ መስራት መቻሉን ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ጀሚላ ስምብሩ በበኩላቸው፣ ሚዲያ ባህልና የቱሪዝም ሀብትን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ በመጥቀስ ለ72ኛዉ የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብ ለሰጡት ሽፋንም አመስግነዋል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክም የዲሞክራሲ ስርዓት መሰረት ለሆነው የኦሮሞ ገዳ ስርዓትን ለመላው አለም ለማስተዋወቅ በሰራቸው ስራዎች በተለይም 72ኛውን የቦረና ኦሮሞ ገዳ የስልጣን ሽግግር (የባሊ ስርዓት ) መረሃ ግብርን በስፋት ሽፋን በመስጠቱ በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እና የኦሮሚያ ባህል ቢሮ በጋራ ባዘጋጁት የምስጋና ስነስርዓት ላይ እውቅናን አግኝቷል።
የእውቅና ሽልማቱንም የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በቦታው ተገኝተው ተረክበዋል።
የቦረና ገዳ ስርዓት የስልጣን ሽግግር (ባሊ ሰነ ስርዓት) ባለፈው ሳምንት በምስራቅ ቦራና ዞን አሬሮ ወረዳ በአርጃ በዳሳ መፈፀሙ ይታወሳል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክም ከስነስርዓቱ ጀማሮ እስከ ማገባደጃ ባለው ጊዜ በተለያዩ አማራጮች ሰፊ ሽፋን መስጠቱ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ውጤታማ ስራውም እውቅናን አግኝቷል።
የገዳ ስርዓት የሰላማዊ የስልጣን ሽግግር፣ የአንድነትና የእኩልነት ተምሳሌት በመሆን በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስ መመስገቡ ይታወሳል።
በጫላ በረካ እና ገመቺስ ምህረቴ